በቤተክርስቲያን መሰብሰባችንን አንተው


በቤተክርስቲያን መሰብሰባችንን አንተው
ጥናት አምስት
የንባቡ ክፍል
ዕብራውያን 10:24-25
ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ፤ በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።

የጥናቱ አላማ

የማሰላሰያ ጥያቄዎች
1. የእብራውያን ፀሐፊ እርስ በራሳቸው እየተገናኙ እንዲተያዩ የሚመክርበት ዋና ምክንያት ምንድን ነው?
2. ለፍቅር መንቃቃትና ለመልካም ስራ መነቃቃት እርስ በርስ ከመገናኘት ጋር ምን የሚያያይዛቸው ነገር አለ?
3. በአንዳንዶቹ የእብራውያን አማኞች መካከል እየተለመደ የመጣው ልምምድ ምንድን ነበር?
መሰብሰባቸውን ያስተዎቸው ነገሮች ምን ሊሆኑ ይችላሉ?
4. ቀኑ ሲቀርብ የሚለው የትኛውን ቀን ነው?
5. እስከ ተባለውስ ቀን አማኞች ሊያደርጉት የሚገባ ነገር ምን እንደሆነ ዘርዝር?

ከሕይወት ማዛመድ
1. በቤተክርስቲያንና በቤት ሕብረት እንዳትሰበሰብና እርስ በርስም እንዳትተያይ የሚያደርጉ እንቅፋቶችህ ምንድን ናቸው?
2. ከሕብረት የመቅረት ልማድ አለህን?
3. ምን ተማርህ?

ፀሎት
1. እርስ በርስ በመገናኘት በፍቅርና በመልካም ስራ መነቃቃትን እንድንለማመድ
2. ከሕብረት የመቅረትን ልማድ እንድናስወግድ
3. በየአካባቢያችን ስለሚጀመሩ የቤት ሕብረቶች

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *